የአበራሽ
ጠባሳ
ዋለልኝ
አየለ
‹‹የአበራሽን
ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም›› የሚለውን
አባባል ታውቁታላችሁ አይደል?
አበራሽ
በእሳት ስትጫወት ተቃጥላ መሰለኝ እንዲህ
የተባለው፡፡ ጎበዝ ወለም ዘለም ሳንል ወደ
ቻይና እንሂድ!
ቻይና
ውስጥ አንዲት ሴት የሆነችው ነገር ለሁላችንም
ትምህርት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ኧረ የእሷ
ደግሞ እኮ ለየት ይላል፡፡ እኛ የምንሰማው
ለረጅም ጊዜ ስልክ ላይ ማፍጠጥ ለአይን ይጎዳል፣
ጊዜ ይገላል ለረጅም ጊዜ በመቀመጥ ለተለያዩ
በሽታዎች ይዳርጋል ነው እንጂ ጭራሽ ይሄ
ይከሰታል ብሎ ማን ገምቶ ነበር?
ኦዲቲ
ሴንትራል ይህን ጉድ ይነግረናል፡፡
አንዲት
ቻይናዊት ሴት የቀኝ እጇ ጣቶች አልታጠፍም፣
አልዘረጋም፣ ለምንም ነገር አልታዘዝም
ብለዋል፡፡ ይህ የሆነው አንዳችም አይነት
የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋ ደርሶባት
እንዳይመስላችሁ፡፡ እጇ ከስማርት ፎን ስልኳ
ላይ አይላቀቅም፤ እንቅልፍ ተኝታ እንኳን
ጣቶቿ ከስልኩ ጋር እንደተጣበቁ ናቸው፡፡
እንዲህ ሆና ለረጅም ጊዜ ከዘለቀች በኋላ ግን
የእጇ ጣቶች እንደታጠፉ ቀሩ፡፡ ነገሩ ከአቅም
በላይ ሆነና በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል
ሄደች፡፡ ጣቶቿ በጣም እንደተጎዱ ተነግሯት
ከዚህ በኋላ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጊ ተብላለች፡፡
ሐኪሞች እንዳሉትም የእጇ ጣቶች ታጥፈው
ስለሚውሉ መታጠፉን ተለማምደውታል፤ መዘርጋት
ነው አዲስ የሆነባቸው፡፡
ጎበዝ
ይሄ ነገር በሁላችንም እንዳይደርስ፡፡
እንደቻይናዊቷ ለዜና ባልበቃም እኔም የደረሰብኝን
ልንገራችሁ፡፡ ገና ፌስቡክ መጠቀም እንደጀምርኩ
ነው፡፡ ያኔ ደግሞ እንደአሁኑ አይነት ስልክ
አልነበረም፡፡ እንደ ኪቦርድ የሚጠቀጠቅ
ስልክ ነበር፡፡ እናም ብርቅ ሆኖብኝ ስጠቀጥቅ
አድሬ የእጄ ጣቶች ውሃ ቋጥረው ነበር፡፡ እንደ
ቻይናዊቷ ቆይቼ ቢሆን እኮ ይቆስል ነበር ማለት
ነው፡፡
በሉ
እንግዲህ ‹‹የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት
አይጫወትም›› የሚለውን አባባል ተግባራዊ
እናድርገውና ከዚች ቻይናዊት ጉዳት እንማር!
No comments:
Post a Comment