ጥበብን
ጥበበኛ ያውቀዋል
ዋለልኝ
አየለ
‹‹ ጥበብ
በእርግማን ብዛት የማትከስም፤ በጭብጨባ
ብዛት የማትለመልም›› የሚለው የበዕውቀቱ
ሥዩም ገለጻ ጥበብን ከምንም በላይ ይገልጻታል፡፡
ከሰሞኑ ይህን የሚያሳይ አንድ ነገር አጋጠመኝ፡፡
አንድ ገጣሚ የግጥም መድብል አሳትሞ ለአንባቢ
አቅርቧል፡፡ ይህ የሆነው ባለፈው ዓመት ነው፡፡
ልጁ የማስተዋወቅ ሥራ አልሠራም፤ መርቁልኝ
አስተዋዉቁልኝም አላለም፡፡ በቃ ጻፈ፤ አሳተመ፤
በዚያው ተወው፡፡
‹‹የመጨረሻውን
ቃል ለጀግናው ተውለት›› እንዲል ሎሬት ጸጋዬ
ገብረመድኅን ይህ ገጣሚ ይወደዳል አይወደድም፤
ይተዋወቃል አይተዋወቅም የሚለውን ለአንባቢ
ትቶታል፡፡ እንደሚታወቀው በአገራችን ከሥራ
በፊት የሚሸጠው ስም ነው፡፡ «ምን
ተጻፈ?»
ሳይሆን
«ማን
ጻፈ?»
የሚለው
ይቀድማል፡፡ የስነ ጽሑፍ መድረኮችንም ማየት
እንችላለን፡፡ ቀድሞ የሚጠቀሰው የታዋቂ
ሰዎች ስም ነው፡፡ ፊልም እንኳን ሲተዋወቅ
ከፊልሙ ይዘት ይልቅ ‹‹እነ እገሌ ያሉበት››
ተብሎ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ደራሲዎች
የመጀመሪያ ሥራቸው ጥሩ ይሆንና ከታወቁ በኋላ
ምንም ነገር ቢጽፉ በሽሚያ ይሸጥላቸዋል፤
ይተዋወቅላቸዋል፡፡
ወደ
ጀማሪዎችም ስንመጣ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ
ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ወደው አይደለም፤ ስማቸው
ስላልተለመደ ሥራቸውም አይታይም፡፡ ደግነቱ
ስም ብቻ እያየ የሚያነብ ሸፋፋ አንባቢ ስለሆነ
ከማጯጯህ ያለፈ ሥራውን ሊመዝን አይችልም፡፡
ሰው ካደነቀው ያደንቃል ሰው ከተቸው ይተቻል፡፡
የፖለቲካው አነሰንና ይህ የመንጋ አካሄድ
ብዙ የኪነ ጥበብ ሥራዎችንም ሰንካላ አድርጓል፡፡
ወደተነሳንበት
እንመለስ፡፡ መዘክር ግርማ የተባለ ወጣት
አንድ የግጥም መድብል አሳትሞ ለንባብ አቅርቦ
ነበር፡፡ ስለመጽሐፉ ብዙም የተባለ ነገር
ሳይኖር ከአንድ ዓመት በላይ ቆየ፡፡ የኔው
ችግር ይሆናል ብዬ አንባቢ ሰዎችን ባማክርም
ከዚህ በፊት እንደማያውቁት ነው የነገሩኝ፡፡
የዚህን ልጅ የግጥም መድብል ግን አንዲት ጥበብ
የገባት ልጅ አገኘችውና በድጋሜ ለምርቃት
በቃ፡፡
ገጣሚ
ረድኤት ተረፈ በግጥሞቿ በብዙዎች ዘንድ
ተደናቂ ናት፡፡ «መስቀል
አደባባይ»
እና
«አንድ
ሐሙስ»
የተሰኙ
የግጥም መድብሎች አሏት፡፡ በመድረክ ላይ
በምታቀርባቸው ግጥሞችም ተወዳጅ ናት፡፡
ይቺ
ገጣሚ የመዘክር ግርማን ግጥም ታገኘዋለች፡፡
መዘክር ግርማ የሚባል ልጅ ፈጽሞ አታውቀውም፡፡
ግጥሙ ግን ግጥም ሆኖ አገኘችው፡፡ የዚህ ልጅ
ግጥም ለምን ሲመረቅ እንዳልሰማችና ለምንስ
በብዙዎች ዘንድ እንዳልታወቀም ግርምት
ፈጠረባት፡፡ የወሰደችው አማራጭ ልጁን አፈላልጎ
ማግኘትና መጠየቅ ነበር፡፡ ልጁን የፈለገችው
ለአንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ መጽሐፉን ራሷ
ለማስመረቅ ፈቃድ እንዲሰጣት ብቻ፡፡ ገጣሚው
መዘክር ግርማ ደሴ ከተማ ተገኘ፡፡ ፈቃደኛም
ሆነ፡፡ መጽሐፉም ሊመረቅ ቀጠሮ ተያዘለት፡፡
በተያዘለት ቀንም ባሳለፍነው ሳምንት ጥቅምት
19
ቀን
2011
ዓ.ም
በብሔራዊ ቴአትር ተመረቀ፡፡
ወደ
ግጥሙ ከመግባታችን በፊት ስለገጣሚው ትንሽ
ነገር ማለት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ
ጊዜ አስተዳደግ፣ የሥራ ሁኔታ፣ የግል ባህሪ
ሁኔታ ከሥራው ጋር ስለሚገናኝ፡፡ ምክንያቱም
ደራሲ የሚጽፈው የኖረውን ሕይወት ነው፡፡
ከዕለት ዕለት የሚያጋጥመውን ነገር ነውና!
መዘክር
ግርማ ደሴ ተወለደ፤ ላሊበላ አደገ፤ አርባ
ምንጭም ትንሽ ኖሯል፡፡ መዘክር ላይ አንድ
ለየት ያለ ነገር አይቻለሁ፡፡ ይህ እኔ
ካስተዋልኩትና ከሰው ከምሰማው አንጻር
ይታይልኝ(በጥናት
የታገዘ አይደለም ለማለት ነው)፡፡
የቋንቋና ስነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ውስጥ
መርጠውት ከሚገቡ ተማሪዎች ይልቅ ያለምርጫቸው
የሚገቡ ይበዛሉ፡፡ ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ
ጀምሮ ያለውን የተማሪዎች ፍላጎትም ብናስተውል
‹‹እኔ ቋንቋና ስነ ጽሑፍ ነው የምማረው››
የሚል አያጋጥመንም፡፡
መዘክር
ጋ ግን ይህ አልሆነም፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ
ቋንቋና ስነ ጽሑፍ መማር ምኞቱ ነበር፡፡ ወደ
ዩኒቨርሲቲ ሲገባም በአንደኝነት የሞላው
ቋንቋና ስነ ጽሑፍ ነው፡፡ የሚወደውንና
የሚፈልገውን የትምህርት ክፍል ተማረ፡፡
በ2006
ዓ.ም
ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋና
ስነ ጽሑፍ ተመረቀ፡፡
ግጥሞቹ
አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳለ የጻፋቸው
ተካተውበታል፡፡ በብዛት ግን ቅርብ ጊዜ
የጻፋቸው ናቸው፡፡ መዘክር ግጥሙን አሳትሞ
ገበያ ላይ ካዋለ በኋላ ብዙ አስተያየት
አግኝቷል፡፡ ያ ሁሉ ሲሆን ካላስተዋወቅኩት፤
በድጋሚ ካላስመረቅኩት አላለም፡፡ አሁን ግን
እሱም ያላሰበው ሆነ፡፡ ገጣሚዋ አፈላልጋ
‹‹እባክህ ላስመርቀው›› አለችው፡፡ በዚህ
ምርቃትም እነ በረከት በላይነህና ሌሎች ታዋቂ
ገጣሚያን ሥራውን ዓይተው አመስግነዋል፡፡
መዘክር
ይህ የግጥም መድብል የመጀመሪያ ሥራው ነው፡፡
እንደተመረቀ በደሴ ኤፍ ኤም እየሠራ ነበር፡፡
አሁን ሥራውን ትቶ እየጻፈ ነው፡፡ የሚሠራው
የስነ ጽሑፍ ሥራዎችን ብቻ ነው፡፡ በቀጣይም
ከግጥም በተጨማሪ ሌሎች የስነ ጽሑፍ ሥራዎችን
እንደሚያቀርብልን በተስፋ እንጠብቃለን፡፡
አሁን
ወደ መጽሐፉ እንግባ፡፡ ወደ መጽሐፉ ስንገባ
ግን እንደ አንድ ግጥም አፍቃሪ አንባቢ ሆኜ
እንጂ እንደ ስነ ጽሑፍ ባለሙያ አይደለም፡፡
በሌላ በኩል ግጥም በስነ ጽሑፍ ባለሙያ እንኳን
አንድ ዓይነት ብያኔ ሊኖረው አይችልም፡፡
ግጥም ሁሉም በአንድ ሃሳብ የሚስማማበት
የሳይንስ ቀመር አይደለም፤ ወይም የተገደበ
ህግ የለውም፡፡ የግጥም ውበቱም ይሄ ነው፡፡
እንኳን አንባቢ ገጣሚው ራሱ ሌላ ጊዜ ቢያነበው
ሌላ ትርጉም ሊሰጠው ይችላል፡፡
ከሽፋኑ
ስንነሳ የገጠር መልከ ዓምድር ይመስላል፡፡
በዚህ መልክዓ ምድር ለይም አንድ ባለአገር
ማይክራፎን ይዞ የሚሄድ ይመስላል፡፡ ይሄ
ነገር ቀላል መልዕክት የለውም፡፡ ገጠር አካባቢ
ብዙ የሚነገሩ ነገሮች አሉ፡፡ እንዲያውም
ገጣሚው ራሱ በመጽሐፉ የምሥጋና ገጽ ላይ
ወይዘሮ ኤልያ ቸኮለ የተባሉ ሰው አመስግኗል፡፡
‹‹ከአንቺው በሰማሁት ቃል ግጥም›› ሲልም
መነሻው የቃል ግጥም እንደሆነ ይነግረናል፡፡
ከዚህ በላይ ደግሞ ራሳቸው ግጥሞቹም ይመሰክራሉ፡፡
በገጠር አካባቢ የሚነገሩ ቃላት አሉበት፡፡
ምንም እንኳን የግጥም ባህሪ ቢሆንም የአጻጻፍ
ሥርዓቱ የንግግር ቋንቋ አለበት፡፡ በተለይም
በግጥም ቅርጽ ዓይን ካየነው ከተለመዱት ለየት
ያለ ነው፡፡ አንዳንዶቹም የራሳችን ዜማ
እንድንፈጥር ያስገድዱናል፡፡ ከተለመደው
የወል ቤት ወይም የሰንጎ መገን ቤት ወይም
የቡሄ በሉ ቤት ወጣ ያሉም አሉ፡፡ እስኪ ይህን
ግጥም እንየው፡፡
ያለፈ
ቀን ዜማ
«ሕይወት
ሃያ ‘ራት ቀን ብትሆን፣ ሃያ ሦስቱን ቀን
ፍጹም ነሽ!
አንዱንም
የተሳሳትሽው፣ ለምን እኔን ጥለሽኝ ሄድሽ?!
ቢሆንም
ቂም የለኝ አየሽ፣ ይሙላልሽ እቴ ስ ‘ተቱም
ልክ
እንዳንቺ ይመር፣ ምሽቱም ንጋቱም፡፡
ምክንያቱም፤
ጥሩ
ቀን -
ሲያልፍ
እንኳ ጠረኑ
የናርዶስ
ነፋስ እንደመሆኑ
ውብ
ዕለት -
ቢያልፍበት
እንኳን መንገዱ
የ‘ሱን
ትዝታ እንደማወዱ
አንቺ
ጋራም ያሳለፍነው
ምንም
ቢያጥር-
ሁለት
መስመር ግጥም ነው፡፡
ሁለት
መስመር ግጥም
ሁለት
ዕድሜ ግድም!»
ግጥም
እንደ ጋዜጣና መጽሔት ጽሑፍ ለሰዋሰው ህግ
ተገዢ አይደለም የሚለውን ታሳቢ እናድርግ፡፡
እርግጥ ነው እንኳን ለሰዋሰው ህግ ለተጠይቅ
(ሎጂክ)
እንኳን
ተገዢ አይደለም፡፡ ያም ሆኖ ግን በሥርዓተ
ነጥብና በራሱ በግጥም ቅርጽ ምቹ ተደርጎ ቢጻፍ
ለአንባቢም ጥሩ ነው፡፡ የተለየ ነገር ይዞ
ካልመጣ የሰዋሰውና የቋንቋን ህግ መጣስ ብቻውን
የግጥም ውበት ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲያም
ግጥም የሰዋሰው ህግ ከሚጥስ ይልቅ የተጠይቅ
ህግ ሲጥስ ውበት ሳይኖረው አይቀርም፡፡
ከላይ
የተጠቀሰው የመዘክር ግጥም ስንኞቹን መከፋፈል
ይቻል ነበር፡፡ በመጀመሪያው አርኬ ሁለተኛው
ስንኝ መጨረሻ ላይ ጥያቄ ምልክትና ቃለ አጋኖን
ይጠቀማል፡፡ አንዱ ይበቃ ነበር፤ ዐረፍተ
ነገሩ ጥያቄያዊ ዐረፍተ ነገር ይመስላል፡፡
ምናልባት ጥያቄውንም ግነቱንም ለመጠቀም
ይሆናል፡፡
ሁለተኛው
አርኬ የመጀመሪያው ስንኝ ላይ ‹‹ቢሆንም
ቂም የለኝ አየሽ፣›› የሚልው ነጠላ ሰረዝ
ከሚሆን ጥያቄ ምልክት ወይም ቃለ አጋኖ ይቀርበው
ነበር፡፡ ሌሎች ግጥሞቹ ውስጥም ያለአስፈላጊ
የሆኑ አራት ነጥብ እና ነጠላ ሰረዝ ይበዛሉ፡፡
አንድ
ግጥም መገምገም ያለበት ከሰዋሰውና ከቅርጽ
አንጻር አይደለም፡፡ እርግጥ ነው የስነ ጽሑፍ
ባለሙያዎቹ ከቅርጽ አንጻርም ይመዝኑታል፡፡
እንደ አንባቢ ሆነን ስናየው ግን ግጥምን
የምንወደው ሃሳቡን ነው፡፡ የመዘክር ግጥሞች
ሃሳብ ያላቸው ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ አንድ
ጊዜ ተነቦ ለመወሰን የሚሆኑ አይደሉም፡፡
ደግመው ሲያነቡት ሌላ ትርጉም ደግመው ሲያነቡት
ሌላ ስሜት የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም
እያዎ ዘይቤ የሚባለው ዓይነት ናቸው፡፡
ትርጉማቸው ያለው ከውስጥ ነው፡፡ ‹‹ምን
ማለት ነው?››
ካልን
በኋላ ወዲያውኑ ይገባናል፡፡ ለምሳሌ ይቺን
ግጥም እንያት፡፡
ወደ
ሞት
«ዓይጥ
ለሞቷ፣ የድመት አፍንጫ
እኔ
ለሕይወቴ፣ የአንቺን ብቻ መምጫ
ይመስለኝ
ነበረ፡፡
ለካ…ዓይጥም
ታመልጣለች፤ ትሾልካለች በጥፍር ሥር
እኔም
ትቸው እኖራለሁ፣ ችላ ብየው የአንቺን ፍቅር፡፡
ምንድነው
እስከዚህ
ቀርተሽ
የሚቀረው
ያላንቺ
መኖር ይቻላል
ያለ
አየር እንደሚኖረው!»
የዚህን
ግጥም ትርጉም ለመረዳት ብዙ ርቀት መሄድ
የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ያለ አየር
መኖር እንደማይቻል ሁሉ ያለ አንቺ መኖር
አልችልም ማለት ነው፡፡ ያለ አንቺ መኖር
ከቻልኩ ያለ አየርም መኖር እችላለሁ እያለ
ነው፡፡ ቀሪ ግጥሞቹን ከመጽሐፉ እንድታነቡ
እየጋበዝኩ በዚህ ግጥም እንሰናበት፡፡
ጅብ
ድሮ እና ዘንድሮ
«የድሮ
ጅብ ትህትናው
ከማያውቁት
ሄዶ ‹‹ቁርበት አንጥፉልኝ?››
ነበረ
ልመናው፡፡
የዛሬ
ጅብ ድፍረቱ
ባለቤቱ
እያየው በዓይኑ በብረቱ
ይሰለቅጥና
ላሚቱን ዘርግፎ
እበረቱ
ያድራል ቁርበቷን አንጥፎ፡፡»
No comments:
Post a Comment